Group Hero

Muslims in Ethiopia

8,858 members

🇪🇹🕌 A group for Muslims in Ethiopia, where we celebrate our faith and cultural diversity.

Share group
Tiro jeyilan biyo

@tiro10171231

20 days ago

hi

Share
Aymen beharu

@aymen_beharu

27 days ago

ለሴቶች ብቻ 🧕🏻
(ወንዶች ከይቅርታ ጋር እናንተን አይመለከትም ተበተኑ 🙂)

ውዷ እህቴ ሷሊህ የሆነ ወንድ ምን አይነት ሴት ለትዳር እንደሚፈልግ ማወቅ ትፈልጊያለሽ? (ምን ጥያቄ አለው? ብለሽ እንደምትመልሽ አልጠራጠርም 😊) እንግዲያውስ ከዚህ በታች መላበስ የሚኖርብሽን 3 አንኳር ባህሪያት ልጠቁምሽ ፤ ባህሪያቶቹ ከአንዱ አንዱ የሚለያዩ ቢሆንም እነዚህን ግን አብዛኛውን ወንድ የሚያመሳስሉ ናቸው።

1- ወንድ ልጅ በተፈጥሮው ባለቤቱ ቁጥብና የተረጋጋች እንድትሆንለት ይመኛል። አለ አይደል ቀለል ቀለል ማለት የምታበዛ ሴት ይንቃል፤ ለትዳር አይደለም እንዲሁ በጋራ ለሚሰራ ስራም አይመርጣትም። ስለዚህ በተቻለ መጠን ቁጥብና ምላሷን የሰበሰበች ሴት ለመሆን ሞክሪ፤ በነገራችን ላይ ይህ ማንነት ለሱ ብቻ ሳይሆን ለራስሽም የውስጥ እርካታን የሚያጎናፅፍ ስለሆነ በደንብ ተግብሪው።

2- ራሷን አግዝፋ የምትመለከትና ሰዎችን የምትንቅ ሴት ወንድ ልጅ አይወድም፤ ለትዳርም አይመርጣትም። ስለዚህ ለሰዎች ክብር ይኑርሽ ተከብረሽ የመኖር ዋስትና በእጅሽ ነው። መልካም ሰው ይቀናጅሽ ዘንድም ቁልፉ ነውና አደራ በደንብ ተጠቀሚበት

3- አላስፈላጊ የአሽሙርና የላግጣ ቦታዎች ላይ እራስሽን አታስቀምጭ፤ ለራሴሽ ክብር ይኑርሽ። ከተራ አሽሙረኛ በላይ የተከበረ ስብእና እንዳለሽ ለራስሽ ንገሪው፤ ላንቺ ባለሽ ክብር ልክ ሰዎች ይመዝኑሻል። በንግግርሽና በተግባርሽ ልክ ሰው ይሰፍርሻል፤ በጭራሽ ቀለሽ አትታይ። አንቺ ከፍ ያለ ስራዎችን መስራት የምትችይ እንደሆነ በማሰብ እራስሽን ቁምነገር ላይ ጥመጅ። እንዲያ ከሆነ አይደለም ሌላ ሰው ይቅርና አንቺ እራስሽ ማንነትሽን ትወጅዋለሽ።

በነገራችን ላይ ፦ እነዚህ ባህሪያት ወንድ ልጅ አንድን ሴት ለትዳር ሲመርጥ ከፊት የሚያደርጋቸው ባህሪያት ቢሆኑም፤ ከትዳር ውጭም የሚያስከብሩ ስብዕናዎች ናቸው።
.
.
.
.
.
ወንዶች በቃ እንዳባታችሁ አደም (ዐለይሂ ሰላም) ናችሁ፤ የተከለከላችሁትን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አትሉም 😉 (ላነበባችሁት ብቻ ነው😄)

6 Likes
1
Share
صلوا على الرسول ﷺ

@Crepaiah

29 days ago

I'm interested in learning Amharic, any female language partner interested in learning Arabic so we can help each other?

2 Likes
1
Share
Niizar Abdurahman

@niiza58545711

29 days ago

Hi

1 Like
Share